የኖብል እንጀራ ድቄት አሠራር
ለ 1 ፓኬት (285 ግራም)
- በመጀመሪያ 1 የታሸገ (285 ግራም) ድቄት በመቀላቀያ ሳህን ዉስጥ ይገልብጡ (የታሸገውን ድቄት ምንም ሣያስቀሩ ሙሉ በሙሉ ይጠቀሙ))
- ዱቄቱን በ 2 ኩባያ (500ሚሊ) ቀዝቃዛ የቧንቧ ዉሀ ማዋሀድ
- በጥቂት ደቂቃ ዉስጥ ሊጡ አረፋ ያወጣል (ኩፍ ይላል)
- አረፉዉ አስኪቀንስ ከ 10 እስከ 15 ደቂቃ ይጠብቁ
- ከዛ በኋላ ከግማሽ ኩባያ (125ሚሊ) ባልበለጠ ዉሀ ማቅጠን
- መጥበሻ ወይም ምጣድ ተጠቅመዉ ትኩስና ጥኡም እንጀራ ጋግረዉ ይመገቡ!

