ኢትዮ ሞደርን ላይፍ ኤል.ኤል.ሲ.

ቤተሰቦቼን ፣ ጓደኞቼን እና ዘመዶቼን እንጀራን ለመጋገር ብዙ ጊዜ ሲያጠፉ መመልከቴ ቀላል እና የተሻለውን መንገድ እንዳስብ አደረገኝ ፡፡ ለአብዛኞቻችን በተለይም በውጭ አገር ለምንኖር ሰዎች ብዙ ጊዜያችንን የሚወስደው ስራ ነው ፡፡ የምንወደውን እንጀራ ለመጋገር ደግሞ በቂ ጊዜ ያስፈልገናል ፡፡

መፍትሄው
ኢትዮ ሞደርን ላይፍ ኤል.ኤል.ሲ. የመጀመሪያውን ኖብል ፈጣን የእንጀራ ዱቄትን እያስተዋወቀ ነው ፡፡ ይህ የመጀመሪያው ፈጣን እና ቀላሉ መንገድ፦ እንጀራን ለመጋገር ይወስድ የነበረውን ጊዜ እና ጉልበት በእጅጉ ያቀልልናል ፡፡ ኖብል ፈጣን የእንጀራ ዱቄት የቤተሰባችንን ወጎች ለማክበር እና ለትውልድ የተላለፈውን እንጀራን የመመገብ ልማድ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችል አዲስ የፈጠራ ዘዴ ነው ፡፡ በተጨማሪም አዲሱ ትውልድ ሥረ መሠረቱን እንዲገነዘብ እና ከምንበላው ጋር እንዲያስተሳስረው የሚያደርግ አመቺ መንገድ ነው ፡፡ የኖብል እንጀራ ዱቄት ከዚህ ዘመናዊ እና ፈጣን ትውልድ የአበላል ዘይቤ ጋር አብሮ የሚሄድ ተወዳጅ ምርጫ ነዉ፡፡

የኖብል ፈጣን የእንጀራ ዱቄት ምንግዜም የማያዝኑበት ምርጫ ነው!