እንጀራን መብላት ይወዳሉ? በአጭር ጊዜ ውስጥ መጋገር ይፈልጋሉ? በጣም ቀላሉን መፍትሄ ለማግኘት በትክክለኛው ቦታ ላይ ነዎት!

ኢትዮ ሞደርን ላይፍ ኤል.ኤል.ሲ.

ምግብ በዓለም ዙሪያ በሁሉም ባህሎች ማንነታችንን፣ ከየት እንደሆንን እና ታሪካችን ምን እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ብዙዎቻችን ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን የራሳችንን ባህልና ወግ ከአዲሱ የአሜሪካ ህይወታችን ጋር አስማምተናል ፡፡ ሆኖም ለዘመናዊ ቤተሰቦቻችን ይህንን የባህል ትስስር ጠብቆ ማቆየት ቀላል አይደለም ፡፡ የተወሰኑትን የምዕራባውያን ባህሎች የተዋሀድነው ሲሆን አብዛኞቹን የአመጋገብ ልምዶቻችንን ግን ጠብቀናል ፡፡ አሁንም እንጀራ መብላት እንወዳለን ሆኖም የምንመራው ፈጣን ህይወት በባህላዊው መንገድ እንጀራ መጋገርን ፈታኝ ያደርገዋል ፡፡ ሥራ ፣ ልጆች ፣ ቤትን መንከባከብ እና የሸቀጣሸቀጥ ግብይት ጊዜያችንን ይወስዳል ፡፡ ስለሆነም ከጥንት የአያቶቻችን ግዜ ጀምሮ ያለውን የእንጀራ አሰራር ለመከተል ጊዜ የለንም ።

ስለ እኛ የበለጠ ያንብቡ